የጅግጅጋ ባይፓስ መንገድ የአስፓልት ስራ ትልቅ የካምፓኒውን ስራ አቅም በግልጽ ያሳየ ነው። ይርጋለም ኮንስትራክሽን በጂግጂጋ ከተማ ሲገነባ የነበረውን የባይፓስ ምንገድ፣ ድልድይ እና ተያያዥ አስፓልት ስራ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ጨርሷል። በፕሮጀክቱ በርካታ ባለሙያዎች አማካሪ መሀንዲሶች፣ የድርጅቱ መሃንዲሶች እና ብቁ ባለሙያዎቻችን የተሳተፉበት ነው።
የፕሮጀክቱ በተለይም የአስፓልስት ስራው መጠናቀቁን የሚገልጹ ባነሮችን ይዘው ሰራተኞች በጋራ ደምቀው ታይተዋል። ይህ የእነርሱ የእያንዳንዱ አሻራ ያረፈበት ከአካባቢው ሞቃታማነት የተነሳ አስቸጋሪ የነበረውን አየር ጸባይ ተቋቁመው የሰሩ መሆኑና ድርጅቱ አስቸጋሪ ሁኔተዎችን ሁሉ ተቋቁሞ የማስፈጸም አቅሙ የሚደነቅ መሆኑን ያሳያል።
የረዳንን እግዚአብሄርን እናመሰግናለን!
ለስራው መሳካት ሌት ተቀን ሲሰሩ የነበሩ ለሳይት መሀንድሶች፣ ማኔጅመንት አካላት፣ ሁሉም ሰራተኞችና ላደረጋችሁልን ከፍተኛ ትብብር በድጋሚ የክልሉ መንግስትና ህ/ሰቡን በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን።



































