HomeFactoryይርጋለም ኮንስትራክሽን በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ የካምፓኒውን አዳዲስ ፋብሪካዎችንና የሰራቸውን ስራዎች አስመረቀ

ይርጋለም ኮንስትራክሽን በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ የካምፓኒውን አዳዲስ ፋብሪካዎችንና የሰራቸውን ስራዎች አስመረቀ

በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ የይርጋለም ኮንስትራክሽን ንብረት የሆነው አዲስ የአቮካዶ ዘይት ምርት ማቀነባበሪያ ፋብሪካና የማር ማቀነባበሪያ ፋብሪካ እንዲሁም የፋብሪካ ፍሳሽ ውሃ ማጣሪያ፣ ፕሮጀክቶች ምረቃ ስነስርዓት ተካሂዷል።

በዛሬው ዕለት ተመርቀው በይፋ ስራ የሚጀምሩ ጎልደን ኦርጋኒክ አቮካዶ ዘይት ፋብሪካ እና ፋሚሊ ማር ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ሲሆኑ የፋብሪካ ፍሳሽ ውሃ ማጣሪያ ደግሞ በጋራ ተመርቋል።

በስነስርዓቱ ላይ በኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመሠረተ ልማትና የግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴታ አቶ ሀሰን ሞሐመድ፣ የሲዳማ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የልማት አጋሮች፣ የይርጋለም ኮንስትራክሽን ባለቤት ኢንጂነር ዘላለም ወ/አማኑኤልን ጨምሮ የኩባንያው ሰረተኞች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ይህንን እውን እንዲናደርግ የረዳን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን፣ በተጨማሪም ሌት ተቀን ሳትሉ ስራዎችን የምትሰሩ ብቁ የኮንስትራክሽን ካምፓኒው ማናጂመንትና ሰራተኞች ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

ይርጋለም ኮንስትራክሽን

Share:

Leave A Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *