የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ፤ በ4 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር የህንፃ ግንባታ ስምምነት በሚኒስቴር መስሪያቤቱ ባለቤትነት በይርጋዓለም ኮንስትራክሽን የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የህንጻው ግንባታ እስከ መስከረም 2019 ዓም ድረስ የሚጠናቀቅ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ግዙፍና በሀገር ውስጥ ኮንትራክተር የሚተገበር መሆኑን ገልፀው፤ በሀገሪቱ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ዕድገት ማሳያና ማስቀጠያ ነው ብለዋል።
ስምምነቱ ላይ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በበኩላቸው፤ የህንፃ ግንባታው የፍትህ አገልግሎትን በአንድ ማዕከል በመስጠት የዜጎችን ህገመንግስታዊ መብት ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው።
ይርጋለም ኮንስትራክሽን በተለያዩ የሀገር አቀፍ ኮንስትራክሽኖችን ጨምሮ የሀዋሳና አ/አ ኮሪደር ልማት ላይ የተሳተፈ አንጋፋ ተቋም ነው።
እንኳን ደስ አለን!















